ተጨማሪ እርምጃዎች

ከሆነ ምን እናድርግ……

እያንዳንዱ የእስራኤል ዜጋ፣ ከ 16 ዓመት ዕድሜው አንስቶ መታወቂያ ካርዱን መያዝ አለበት።
መታወቂያ ካርድ ከሌለዎት ለኦሊም (Olim) የሚሰጠውን የመጀመሪያ መታወቂያ ካርድዎ ሊኖርዎት ይገባል።
እንዴት?
እባክዎን የኦንላይን የቀጠሮ ስርዓት የሆነውን myVisit ይጠቀሙ
እና በኔታኛ ቅርንጫፍ (13 Remez St., Netanya) ቀጠሮ ይያዙ።
እባክዎን እነዚህን ከእርስዎ ጋር ይዘው ይምጡ፦
የውጭ ፓስፖርት
የኢሚግሬሽን የምስክር ወረቀት
የልደት ምስክር ወረቀት
በመመለሻ ህግ (Law of Return) መሰረት ብቁ መሆንዎን የሚመሰክሩ ሰነዶች
የጋብቻ የምስክር ወረቀት፣ የፍቺ የምስክር ወረቀት ወይም የመበለት የምስክር ወረቀት፣ ወይም ከእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ለአንዱ ማረጋገጫ የሚሆን የግል መግለጫ።
የህዝብ መመዝገቢያ አባሪ፦ የመታወቂያ ካርድዎን በቤን ጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ ካልተቀበሉ፣ “የህዝብ መመዝገቢያ ቅጽ” ይደርስዎታል። ይህ የመታወቂያ ቁጥርዎን እና የግል ዝርዝሮችዎን ያያዘ ቅጽ ነው። ከህዝብ፣ ኢሚግሬሽን እና ድንበር ባለስልጣን ቋሚ መታወቂያ ካርድ ለመቀበል ከአሊያ (Aliyah) እና ውህደት ሚኒስቴር ተወካይ ቅጹን ይቀበላሉ።
በጣም አስፈላጊ!
መታወቂያ ካርድ ለመያዝ ከሚጠይቀው ህጋዊ መስፈርት በተጨማሪ፣ የተለያዩ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶችን፣ የገንዘብ ድጋፍ ቅርጫት ወዘተ ማግኘት መቀጠል እንዲችሉ የመታወቂያ ካርድ ማግኘቱ አስፈላጊ ነው።

Teudat Oleh (የኢሚግሬሽን የምስክር ወረቀት) በአሊያህ እና ውህደት ሚኒስቴር የኦሌህ (Oleh) ሁኔታ ላላቸው ሰዎች የተሰጠ ቡክሌት ነው።
ቡክሌቱ ለቤተሰብ አንድ እንጂ ለእያንዳንዱ ግለሰብ አንዳንድ አይደለም፣ እናም በውህደት ጊዜ የተገኘውን እርዳታ እና ጥቅማጥቅሞችን ለማስታወስ ይጠቅማል።
ዕድሜያቸው ከ 21 ዓመት በላይ የሆናቸው ልጆች የተለየ የኢሚግሬሽን የምስክር ወረቀት ይወስዳሉ።
ወደ አሊያህ እና ውህደት ሚኒስቴር ወይም ማዘጋጃ ቤት የቅበላ ክፍል በሚሄዱበት ጊዜ ሁሉ እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ባንክ፣ ወደ አርኖና/Arnona (የከተማ ግብር) መምሪያ በሚሄዱበት ጊዜ፣ ልጆችዎን ለትምህርት ማዕቀፎች ሲያስመዘግቡ እና ሌሎችም፣ የኢሚግሬሽን የምስክር ወረቀትዎን ማሳየት ያስፈልግዎታል።

እንዴት?
ቀጠሮዎችን በመደወል፦
1599-500905
ወይም በኦንላይን የቀጠሮ ስርዓት – myVisit መያዝ ይቻላል
እባክዎን እነዚህን ከእርስዎ ጋር ይዘው ይምጡ፦
መታወቂያ ካርድ/ፓስፖርት ወይም ሌላ ተዛማጅ ሰነድ።
አድራሻ፦
3 Bareket Street፣ 9ኛ ፎቅ፣ ኔታኛ

ለአንዱ የ kuppot holim (HMOs) መመዝገብ የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ቅድመ ሁኔታ ነው፦

ክላሊት (Clalit) የጤና አገልግሎቶች፦ *2700 ወይም 03-9405350 መቃብ (Maccabi) የጤና አገልግሎቶች፦ *3555* ወይም 1700-50-53-53 Meuhedet የጤና አገልግሎቶች፦ * 3833 Leumit የጤና አገልግሎቶች፦ *507 ወይም 1-700-507-507

በአንዱ የፖስታ ባንክ ቅርንጫፎች እና በኋላ ከመረጡት የ kuppat holim ቅርንጫፎች በአንዱ።
በእስራኤል ፖስት ድህረ ገጽ ላይ አስቀድመው ቀጠሮ እንዲይዙ እንመክራለን እዚህ ጠቅ ያድርጉ
ወይም በኦንላይን የቀጠሮ ስርዓት – በአቅራቢያዎ ባለው የፖስታ ቤት ቅርንጫፍ ቀጠሮ ይያዙ
እባክዎን እነዚህን ከእርስዎ ጋር ይዘው ይምጡ፦
– መታወቂያ ካርድ
– የኢሚግሬሽን የምስክር ወረቀት
በጣም አስፈላጊ!
• በሚያስፈልግዎት ጊዜ የህክምና አገልግሎቶችን ማግኘት እንዲችሉ በተቻለ ፍጥነት መመዝገብ አስፈላጊ ነው
• በፖስታ ቤት መመዝገብ በጥሬ ገንዘብ የሚከፈል ክፍያ አለው
• ከአሊያህ (Aliyah) ቀንዎ ጀምሮ በ 90 ቀናት ውስጥ መመዝገብ አለብዎት። ከዚያ በኋላ በ 68 Herzl St., ኔታኛ ወደሚገኘው የእስራኤል ብሔራዊ መድህን ተቋም ቅርንጫፍ መሄድ ያስፈልግዎታል።
ቀጠሮ ለመያዝ እዚህ ጠቅ ያድርጉ