በከተማ ውስጥ አገልግሎቶችን ለማግኘት ቀጣይ እርምጃዎች

የሚፈልጉትን መረጃ በሙሉ ለእርስዎ ሰብስበናል።

ቅናሽ (ለ Olim ብቻ)፣ በደንቦቹ መሠረት። ከ Aliyah ቀንዎ ጀምሮ ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ቅናሹን አንድ ጊዜ ብቻ እና ለአንድ ዓመት ብቻ የማግኘት መብት አለዎት።
እንዴት?
ወደ ኔታኛ ማዘጋጃ ቤት ገቢዎች ክፍል ቢሮዎች መሄድ አለብዎት፡ 4 Hatzoran St.፣ Elevator 7፣ 2nd Floor

ለህዝብ ክፍት የሚሆኑት፦
ከእሑድ-ሐሙስ ከ 8:00 a.m. – 1:00 p.m ድረስ
ረቡዕ ከ 4:30 p.m. – 6 p.m. ድረስ
ወይም
የኦንላይን ጥያቄ ማስገባት ይችላሉ
ይህን ለማድረግም እዚህ ጠቅ ያድርጉ

እባክዎን እነዚህን ከእርስዎ ጋር ይዘው ይምጡ፦
የኢሚግሬሽን የምስክር ወረቀትዎ፣ መታወቂያ ካርድዎ እና በስምዎ ያለን የኪራይ ውል። አፓርታማው የእርስዎ ከሆነ እና ከእርስዎ Aliyah በፊት ንብረቱን የገዙ ከሆነ፣ እባክዎን ፓስፖርትዎን ይዘው ይምጡ።
በጣም አስፈላጊ!
ቅናሾቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊለዋወጡ የሚችሉ እና በመንግስት ደንቦች እና መመሪያዎች መሰረት የሚደረጉ ናቸው።
እባክዎን ያስተውሉ፦ ልጆቻችሁን በትምህርት ተቋማት ለማስመዝገብ ካሰቡ፣ በተመሳሳይ ጊዜ ከገቢዎች መምሪያ የንብረት ባለቤት ፈቃድ እንዲያገኙ እንመክራለን። ይህ ተመላሰው መጠየቅ ያድንዎታል።

የኔታኛ አለም አቀፍ Ulpan
ይህ በከተማው ውስጥ ለሰላሳ ዓመታት ያህል ሲሠራ የቆየ የዕብራይስጥ ትምህርት ቤት ነው። በትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶች ትምህርት ክፍል ፔዳጎጂካል ቁጥጥር ስር ሲሆን ከኔታኛ ማዘጋጃ ቤት እና ከ Aliyah እና ውህደት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ይሠራል።
እንዴት?
እባክዎን አለምአቀፍ ኡልፓን (International Ulpan)፣ ከእሁድ – ሐሙስ፣ ከ 10:00 a.m. – 1:00 p.m ድረስ ያነጋግሩ።
በዕብራይስጥ፣ በፈረንሳይኛ ወይም በእንግሊዝኛ ከአንድ ሰው ጋር ለመነጋገር፣ እባክዎን በ 09-8341223 ይደውሉ
በዕብራይስጥ ወይም በሩሲያኛ ከአንድ ሰው ጋር ለመነጋገር፣ እባክዎን በ 09-8341113 ይደውሉ
አድራሻ፦ 71 Harav Kook St., ኔታኛ
እባክዎን እነዚህን ከእርስዎ ጋር ይዘው ይምጡ፦
የኢሚግሬሽን የምስክር ወረቀትዎን፣ መታወቂያ ካርድዎን እና በቀደመው ደረጃ ላይ ከ Klita አማካሪ የተቀበሉትን የመመዝገቢያ ቫውቸር።
በጣም አስፈላጊ!
ቀደም ሲል አስተዳደግዎ በዕብራይስጥ ቋንቋ ከሆነ፣ ምን ዓይነት ደረጃ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ፈተና ለመፈተን ሊጠይቁ ይችላሉ።
አገልግሎቱ የታሰበው ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆነ Olim ነው።

በ Aliyah ላይ በተለያየ ዕድሜ ላይ ካሉ ልጆች ጋር መጡ? ለተገቢው ማዕቀፎች እነሱን ለማመዝገብ ጊዜው አሁን ነው።
የእስራኤል የግዴታ ትምህርት ህግ ከቅድመ ትምህርት ቤት 3 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ እስከ 18 ዓመት ዕድሜ ድረስ (ከልዩ ትምህርት እስከ 21 ዓመት) ይተገበራል።
በትምህርት ክፍል ውስጥ አራት የተለያዩ የምዝገባ መምሪያዎች አሉ፡-
1. ቅድመ ልጅነት – እስከ 3-6 ዓመት ዕድሜ ድረስ
2. አንደኛ ደረጃ ትምህርት – ከ1-6ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች
3. ድህረ-አንደኛ ደረጃ ትምህርት – ከ 7-12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች
4. ልዩ ትምህርት – ልዩ ፍላጎት ላላቸው ልጆች፣ ዕድሜያቸው ከ 3-21 ዓመት ለሆኑ ልጆች ኃላፊነት ያለው
እንዴት?
የሚመለከታቸውን የትምህርት መምሪያዎች ከማነጋገርዎ በፊት፣ እባክዎን ከገቢዎች ክፍል “የንብረት ባለቤት ፈቃድ” ያግኙ (ያለዚህ ፈቃድ መመዝገብ አይችሉም)።
ይህንን ለማድረግ፣ እባክዎን የገቢዎች ክፍልን ይጎብኙ፡ 4 Hatzoran St.፣ አሳንሰር 7፣ 2ኛ ፎቅ፣ ኔታኛ
ለህዝብ ክፍት የሚሆኑት፦
ከእሑድ-ሐሙስ ከ 8:00 a.m. – 1:00 p.m ድረስ
ረቡዕ ከ 4:30 p.m. – 6 p.m. ድረስ
ፈቃዱ ከተሰጠ በኋላ፣ እባክዎን ከሚከተሉት ሰነዶች ጋር ወደሚመለከተው የምዝገባ ክፍል ይሂዱ።
የኢሚግሬሽን ምስክር ወረቀት፣ በንብረቱ ባለቤት ፈቃድ መሰረት አሁን ያለው የመኖሪያ አድራሻ ያለው መታወቂያ ካርድ፣ እና ካለፈው የትምህርት ዘመን የተሰጠ የሪፖርት ካርድ።
12 Tchernichovsky St., 1 ኛ ፎቅ፣ ኔታኛ።
ለተጨማሪ መረጃ፣ እዚህ ይጫኑ
በጣም አስፈላጊ!
የንብረት ባለቤት ፍቃድ መውጣት ካልቻሉ፣ በከተማው ውስጥ እየኖሩ እንደሆነ የሚገልጽ መግለጫ ከጠበቃ ይዘው መምጣት ይችላሉ።
እባክዎን ያስተውሉ፦ ይህ አገልግሎት የሚቀርበው በድጎማ ዋጋ ሲሆን በኔታኛ በሚገኘው ቤእት ሚሽፓት ሃሻሎም/Beit Mishpat Hashalom/ (የማጅስትሬት ፍርድ ቤት) ማግኘት ይቻላል።
57 Herzl St. (መሬት ወለል)፣ ኔታኛ

ጤና እና ኩፖት ሆሊም (kuppot holim, HMOs)
ጤናዎን መንከባከብዎ ለእኛ አስፈላጊ ነው!
በአውሮፕላን ማረፊያው ውስጥ HMO ን ለመምረጥ ቅጹን እንደሞሉ በማሰብ፣ ማድረግ የሚያስፈልግዎት፣ በከተማው ካሉት ቅርንጫፎች ከአንዱ የ kuppat holim አባልነት ካርድዎን መውሰድ ብቻ ነው።
እንዴት?
በቀላሉ ለተመዘገቡበት የ kuppat holim ይደውሉ እና በአቅራቢያዎ ያለውን ቅርንጫፍ አድራሻ ያግኙ – ካርዶችዎን እዚያ ማግኘት ይችላሉ።

 


ክላሊት (Clalit) የጤና አገልግሎቶች፦ *2700 ወይም 03-9405350

መቃብ (Maccabi) የጤና አገልግሎቶች፦ *3555* ወይም 1700-50-53-53

Meuhedet የጤና አገልግሎቶች፦ * 3833

Leumit የጤና አገልግሎቶች፦ *507 ወይም 1-700-507-507